Southwest Communications
swc79.bsky.social
Southwest Communications
@swc79.bsky.social
We are delivering you an update and reliable information about Southwest Ethiopia Peoples Regional state activities, news, and national & international issues
ብልፅግና ታሪክን ወደ ሀብት፣ ቅርስን ወደ እሴት የቀየሩ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ማሳካት የቻለ ፓርቲ ነው - የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ተመስገን ጥሩነህ

ብልፅግና ፓርቲ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደርበትን የምርጫ ማኒፌስቶ እና በምርጫው የሚወከልበትን ምልክት ይፋ አድርጓል።

የብልፅግና ምክትል ፕሬዚዳንት ተመስገን ጥሩነህ በዚሁ ወቅት በ6ኛው እና በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫዎች መካከል ፓርቲው እውን ያደረጋቸውን ሁለንተናዊ ስኬቶች በንፅፅር አቅርበዋል።
February 10, 2026 at 2:33 PM
የ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት “የስንዴ ነዶ” ነው። የስንዴ ነዶ የመደመር፣ የአንድነት፣ ትብብርና የሉአላዊነት መገለጫ ነው።

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!
February 10, 2026 at 2:32 PM
ከ11ሺህ በላይ ማኅበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርግ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት ተመረቀ።

በዳውሮ ዞን ከጪ ወረዳ፣ የከጪ ከተማ የንጹሕ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በገተገኙበት ተመርቋል።

ፕሮጀክቱ በከጪ ከተማ ለረጅም ጊዜ ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግርና የህዝብ ጥያቄ ሆኖ የቆየውን የንጹህ መጠጥ ውሃ እጥረት በዘላቂነት የሚፈታ እንደኾነም ታምኖበታል
February 10, 2026 at 12:54 PM
ባለፉት 6 ወራት ከ2 ነጥብ 5 ቢልዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ ገለጸ።

የመምሪያው የ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻፀም ግምገማ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ መንፈቅ 2 ቢሊዮን 572 ሚልዮን 546 ሺህ ብር በላይ ለመሰብሰብ መታቀዱ ይታወሳል።
February 10, 2026 at 12:53 PM
የአፍሪካ መሪዎች በአዲስ አበባ - ከውኃ ዋስትና እስከ አዲሱ ትውልድ የፖለቲካ ተሳትፎ

መዲናዋ አዲስ አበባ የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም የ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤን ታስተናግዳለች።

ይህ ጉባኤ በአህጉሪቱ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ "አጀንዳ 2063" መሠረት አስተማማኝ የውኃ እና የንፅህና አቅርቦትን በማረጋገጥ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን፣ ከፍተኛ የአህጉሪቱ መሪዎችም በጉዳዩ ላይ ይመክራሉ።
February 10, 2026 at 12:37 PM
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)÷ በዳውሮ ዞን፣ ማረቃ ወረዳ በክልሉ የመስኖ ኤጄንሲ የተሰራውን የውኒ አነስተኛ መስኖ መርቀው ከፍተዋል።

ከ144 ሄክታር የማልማት አቅም ያለው የመስኖ ፕሮጀክት የተገነባው ከ75 ሚሊዮን በሚጠጋ የክልል መንግሥት የበጀት ድጋፍ ነው።

ፕሮጀክቱ የ5.7 ኪሎሜትር ዋና የውሃ ካናል የመስመር ዝርጋታ እና ሌሎች የስትራክቸርና መካኒካል ሥራዎችን ያካተተ ነው
February 10, 2026 at 8:10 AM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሰው አልባ ፖሊስ አገልግሎት ወይም ስማርት ፖሊስ አገልግሎት ዛሬ አስጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የሰው አልባ ፖሊስ አገልግሎት ዜጎች የፖሊስ አገልግሎትን በተሻለ ፍጥነት እና በቴክኖሎጂ ታግዘው እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ብለዋል።

አገልግሎቱ ለፖሊስ ፈጣን እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችለው እና የወንጀል መከላከል ስራውን ያቀላጥፋል
February 10, 2026 at 8:07 AM
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በበጋ መስኖ የሚለማው የስንዴ ማሳ ሽፋንና ምርታማነት በየዓመቱ እያደገ መጥቷል።

ይህ ልማት የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ ባለፈ፣ የገቢ አቅማቸው እንዲጎለብት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።

በክልሉ ካፋ ዞን ሺሾ እንዴ እና ጊምቦ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮች፣ በአካባቢያቸው የተገነቡ የመስኖ አውታሮችን በመጠቀም ስንዴን በኩታ ገጠም (ክላስተር) እርሻ እያለሙ ነው።
February 10, 2026 at 8:05 AM
የማጃንግ ብሔረሰብን የቀደሙ የባህል እሴቶችና ቋንቋ ለማነቃቃት እና ለልማት ለማዋል ያለመ ታላቅ የባህልና የቋንቋ ሲምፖዚየም የካቲት 4 እና 5 በቴፒ ከተማ እንደሚካሄድ የዝግጅቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዮሐንስ በንዲ ገለጹ።

አቶ ዮሐንስ እንደገለጹት፣ ለሲምፖዚየሙ የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በሙሉ ተጠናቀዋል

የሲምፖዚየሙ ዋና ዓላማ ለረዥም ጊዜ ተዘንግተው የነበሩ የማጃንግ ብሔረሰብ ባህላዊ እሴቶችንና የአኗኗር ዘይቤዎችን እንደገና ማንቃት መሆኑን ጠቁመዋል
February 10, 2026 at 8:04 AM
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የክልልና የኮንታ ዞን አመራሮች የአመያ ከተማ የኮሪደር ልማት ፣የጪዳ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ እንዲሁም ሌሎች የልማት ስራዎች ጎብኝተዋል።

ክልሉ ተከማችተው የነበሩ ዕዳዎችን በማቅላል ወደ ምንዳነት በማሸጋገር በርካታ የልማት ስራዎችን በማስመረቅና አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ የመሰረት ድንጋይ በመስቀመጥ የህዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ይገኛል።
February 10, 2026 at 8:02 AM
ጉባኤውን ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የክልሉ ምክር ቤት አስታወቀ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን የካቲት 5 እና 6 እንደሚያካሄድ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ገልፀዋል።

የ2018 ዓ.ም ግማሽ ዓመት የአስፈፃሚ አካላት ስራ ሪፖርትን ጨምሮ ሌሎች አጀንዳዎች በጉባኤው እንደሚቀርቡም አመላክተዋል።
February 9, 2026 at 10:21 AM
ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ተችሏል - ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

ግንባታው ከ10 ዓመታት በላይ የተጓተተው የአመያ ኢንዱስትሪ ማዕከል ተመርቀው ተከፈተ።

የማምረቻ ማዕከል መገንባት በክልሉ የኢንዱስትሪ ሽግግር ለማሳለጥ የጎላ ፋይዳ እንዳለው ነው በምርቃት ወቅት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የገለጹት።
February 9, 2026 at 10:20 AM
የሀገራችን ብሩህ ተስፋ የሚጀምረው ከእርስዎ ድምፅ ነው

የሀገራችንን ዕድል ለመወሰን እና የነገዋን ኢትዮጵያ በጋራ ለመገንባት የመጀመሪያው እርምጃ የመራጮች ምዝገባ ነው።

ድምፅ መስጠት መብትዎ ብቻ ሳይሆን ለሀገር የሚከፈል ታላቅ ውዴታም ጭምር ነው

የምዝገባ ጊዜ፦ ከየካቲት 7 እስከ መጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም

በቀኑ በመመዝገብ፣ ነገ የሀገርዎን መጻኢ ዕድል በድምፅዎ ይወስኑ! የምዝገባ ካርድዎን መውሰድዎን አይዘንጉ

"ዛሬ እንመዝገብ፤ ነገ በድምፃችን እንወስን!"
February 9, 2026 at 10:18 AM
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ በኮንታ ዞን አመያ ከተማ በክልሉ መንግሥት የተገነባውን የአምራች ኢንዱስትሪ የማምረቻ ማዕከል መርቀዋል።

ፕሮጀክቱ በቀድሞው የደቡብ ክልል ጊዜ ተጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ግንባታው የተጓተተ ቢሆንም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምሥረታ ማግስት÷ የክልሉ መንግሥት ፕሮጀክቶችን አጠናቀው ለኅብረተሰቡ ተገቢውን አግልግሎት እንዲሰጡ በሰጠው ልዩ ትኩረት ተጠናቆ ለምረቃ በቅቷል
February 9, 2026 at 10:17 AM
ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ግንባታቸው የተጠናቀቁ የልማት ፕሮጀክቶችን ለማስመረቅ አመያ ከተማ ገቡ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ተገንብተው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን ለማስመረቅ ኮንታ ዞን ገብተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዞኑ በሚኖራቸው ቆይታ÷ በክልሉ መንግሥት የተከናወኑ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ያስመርቃሉ።
February 9, 2026 at 10:14 AM
ላለፉት 4 ዓመታት ለተጨማሪ 490 ሺህ ነዋሪዎች የንፁህ መጠጥ ውሃ ማድረስ እንደተቻለ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ገለፀ።

‎የቢሮ ሀላፊ የሆኑት ኢንጂነር በየነ በላቸው የንፁህ መጠጥ ውሃ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት የሚጠይቅ በመሆኑ የተለያዩ አጋር አካላት ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠይቀዋል።

‎በክልሉ የንፁህ መጠጥ ውሃና ሌሎች መሰረት ልማት አነስተኛ እንደነበረ ነው ኢንጅነር በየነ በላቸው ገልጸዋል ‎
February 9, 2026 at 10:13 AM
የክልሉ ‎መንግስት የህዝብ ተጠቃሚነትን ሊያረጋግጡ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፦‎ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

‎‎በካፋ ዞን ከ22 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን ‎ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ መርቀው ከፍተዋል።
February 9, 2026 at 10:11 AM
በኮንታ ዞን አስተዳደር ከ121 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የጪዳ ከተማ አስተዳደር እና የኤላ ሀንቻኖ ወረዳ አስተዳደር ህንፃ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።

በምረቃው መርሀ-ግብር የክልሉ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ነጋ አበራ፣ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል ሲል የኮንታ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል
February 9, 2026 at 10:11 AM
የለውጡ መንግሥትና ፓርቲዉ በልማት ወደ ኋላ የቀሩ አካባቢዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላል ፦ ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ (ዶ/ር) በካፋ ዞን የቢጣ ዳካ መንገድ፣ የሜኒ ወንዝ ድልድይ እንዲሁም የቢጣ ገነት ከተማ የንጹህ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክቶችን መርቀው ከፍተዋል።
February 9, 2026 at 10:04 AM
የሸኮ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የህንጻ ግንባታ የመሠረተ-ድንጋይ ተቀመጠ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት፣በቤንች ሸኮ ዞን በሸኮ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ባለሁለት ወለል ሕንፃ ግንባታ በይፋ ተጀመረ። ለዚህም ግንባታ የመሠረተ-ድንጋይ ያስቀመጡት የክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ናቸው።
February 9, 2026 at 10:03 AM
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለአፍሪካ ሀገራት ተምሳሌት ለማድረግ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ሊሰሩ ይገባል ፦ አቶ ፍቅሬ አማን

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትና በክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ትብብር የተዘጋጀ የባለድርሻ አካላት ስልጠናና የቀጣይ አቅጣጫ መድረክ በሚዛን ተካሄደ
February 9, 2026 at 10:01 AM
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ (ዶ/ር) በካፋ ዞን የቢጣ ዳካ መንገድ፣ የሜኒ ወንዝ ድልድይ እንዲሁም የቢጣ ገነት ከተማ የንጹህ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክቶችን መርቀው ከፍተዋል።

የቢጣ ዳካ መንገድና የሜኒ ወንዝ ድልድይ ፕሮጀክት 94 ሚሊዮን ብር በክልሉ መንግስት እና 4 ሚሊዮን ብር በህብረሰተብ ተሳትፎ በአጠቃላይ በ98 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ ሲሆን መንገዱ 51 ኪሎሜትር ሲሆን ድልድዩ 22 ሜትር እርዝማኔ አለው።
February 9, 2026 at 9:59 AM
ባለፉት ዓመታት የእንስሳት ሀብት ልማትን ለማሳደግ የተከናወኑ ዘርፈ-ብዙ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገባቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት ይፋ የተደረገ ሀገራዊ መርሃ-ግብር ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም የእንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ነው።
February 9, 2026 at 9:56 AM
የልማት ክፍተቶችን ለመፍታት በተሰሩ ሥራዎች ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛሉ :- ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በምዕራብ ኦሞ ዞን የባቹማ ኮንስትራክሽን እና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።

በክልሉ በመንግሥትና ፓርቲው መሪነት ባለፉት ዓመታት የልማት ውስንነት ባለባቸው አከባቢዎች የልማት ክፍተቶችን በመፍታት ረገድ ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግቧል ብለዋል
February 9, 2026 at 9:55 AM
ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት በ68 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባዉን የባቹማ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ተመረቀ

የኮሌጁ ግንባታ በ2011 ዓ/ም በቀድሞው የደቡብ ክልል ተጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች የተቋረጠ ሲሆን፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት በ2017 ዓ/ም ውሉን እንደገና በማሳደስ ግንባታውን በድጋሚ በማስጀመር ቅርብ ድጋፍና ክትትል በማጠናከር በአንድ ዓመት ውስጥ ግንባታውን አጠናቅቆ ለምረቃ አብቅቷል።
February 9, 2026 at 9:53 AM